ይህ የማሳያ መለያ ነው። እባክዎ ምንም አይነት ሚስጥራዊ መረጃ አያስገቡ።

ከድርጅታችን መርሆዎች አንዱ የሚከተለው ነው፦ 

“እኛ ተግባራዊ የሆነውን ህግና የውስጥ መመሪያዎችን እንከተላለን።” 


በህጋዊ አካሄዳችን አማካኝነት እርስዎ በእኛ ላይ መተማመን እንደሚችሉ እናረጋግጣለን። ስለዚህ ተስማምነት (ኮምፕላያንስ) ለዘላቂ የንግድ ስኬታችን ወሳኝ የግንባታ ክፍል ነው።

ስለዚህ ሊከሰቱ የሚችሉ ስህተቶችን በተነጣጠረ መንገድ እና በተቻለ ፍጥነት ለመቆጣጠር ለእኛ አስፈላጊ ነው። ይህንንም የምናሳካው በአንድ በኩል ሊኖሩ ስለሚችሉ ስህተቶች ሪፖርቶችን በመቀበል ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ድርጅቱን የሚመለከቱ ተስማምነት-ነክ ጥያቄዎች ላይ ምክር እንዲያገኙ እድል እናቀርባለን። 

ለዚህ ግብ ይህ የመስመር ላይ ሪፖርት ማቅረብ ስርዓት ለእርስዎ ተዘጋጅቷል። ሪፖርቶችን ለማቅረብ ወይም ምክር ለመፍለግ ወደ እሱ ቢመለሱ, ጉዳይዎ በጥብቅ ሚስጥራዊነት ይያዛል። 

እባክዎ ይህን የመስመር ላይ ሪፖርት ማቅረብ ስርዓት በኃላፊነት ይጠቀሙ። ሌሎችን ለማጋለጥ ተግባራዊ ሊሆን አይገባም። በመሆኑም እባክዎ በእውቀትዎ እና በእምነትዎ መጠን ትክክለኛነታቸውን የተረዱበትን መረጃ ብቻ ያቅርቡልን።

ይህ የመስመር ላይ ሪፖርት ማድረጊያ ስርዓት ለኮምፕላያንስ ጉዳዮች ሪፖርት ለማድረግ ተዘጋጅቷል። እባክዎ ሌሎች ጉዳዮች በዚህ መስመር ሊስተናገዱ እንደማይችሉ ልብ ይበሉ።

ከዚህ የመስመር ላይ የጠቋሚዎች ስርዓት በተጨማሪ ለሪፖርቶች ወይም ለጥያቄዎች ያሉ ሌሎች ተጨማሪ መስመሮች (ለምሳሌ የተስማምነት ኃላፊዎች) እንደተጠበቁ ይቆያሉ።

የጠቋሚዎች ስርዓታችን እርስዎን እንዴት እንደሚጠብቅ

  • ስርዓቱ ከሁለት ጎን ሊደረስበት እንደሚችል መቆለፊያ ሳጥን ይመስላል።
  • የእርስዎ መረጃ እና ፋይሎች በተመሰጠረ መልኩ ይተላለፋሉ።
  • እርስዎን ለመለየት የሚያስችል መረጃ አንሰበስብም ወይም አንቀበልም።
  • ወደ እርስዎ ተመልሶ በቴክኒካዊ መንገድ መከታተል አይቻልም።